የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ስምዖን የመጀመሪያውን የአጥቢያ ጉብኝት አደረጉ

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ስምዖን ሙላት የቤተ ክርስቲያኒቱ ዋና ጸሐፊ ከሆኑ በኁዋላ የመጀመሪያውን የአጥቢያ ጉብኝት በሽሬ ቃለ ሕይወት አድርገዋል። ይኸው ጉዞም በዋና ጸሐፊው የረጅም ዘመን ወዳጅ እና የስራ ባልደረባ ዶ/ር ፍሬው እና የትግራይ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን መሪና የሽሬ ቃለ ሕይወት መጋቢ በሆኑት ፓ/ር ተመስገን አስተባባሪነት የተደርገ ነው። በዚሁ ጉዞ ዶ/ር ፍሬው እና የኢቲሲ መምህር የሆኑት የዲዳስኮ አገልግሎት አስተባባሪ ወንድም እንዳሻው ነጋሽ ተካተው በሽሬ አገልጋዮች ማሰልጠኛ ኮሌጅ ቢሮ ለኤርትራውያን ስደተኞች እና ኢትዮጵያውያን የወንጌል አገልጋዮችስልጠና ሰጥተዋል። ዶ/ር ስምዖንም ፈጣን ዕድገት በማሳየት ዘርፈ ብዙ አገልግሎትን በሽሬና ሰሜናዊው የሃገራችን ክፍል በመስጠት ላይ ባለችው የሽሬ ቃለሕይወት ቤተ ክርስቲያን የሰንበት አምልኮ ላይ አስተምረዋል።