የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን 58ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ተካሄደ

 

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን 58ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ከሚያዝያ 3 -5 /2011ዓ.ም በቤተ ክርስቲያኒቱ ኩሪፍቱ ማዕከል ተካሄደ።
ይኸው ዓመታዊ ጉባዔ በተያዘለት ምርሃ ግብር መሰረት ለሁለት ቀናት የተካሄደ ሲሆን በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ አቶ ንጉሤ ቡልቻ በትጋባዥ አገልጋይነት ተገኝተው በእውነተኛ አንድነት ቤተ ክርስቲያንን ስለመምራትና ስለማገልገል አስተምረዋል።
በመቀጠልም በቤተ ክርስቲያኒቱ ቦርድ ተዘጋጅተው በቀረቡ የቤተ ክርስቲያኒቱ ዋና ጽሕፈት ቤት እና በልማት ኮምሽን ጽሕፈት ቤት ለዪ ለዩ አጅንዳዎች ላይ በመመከር ውሳኔዎቸ ተላለፈዋል። በዚሁ ወቅትም የቤተ ክርስቲያኒቱ እና የልማት ኮሚሽኑ የሥራ እና የሒሳብ ሪፖርቶች ቀርበው በጉባዔው ተገምግመዋል።

 

 

 


በሁለተኛ ቀን በነበረው ጉባዔ ላይም ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመጪዎቹ ዓመታት የሚመሩ መሪዎች ምርጫ የተካሄደ ሲሆን
ዶ/ር ኢያሱ ኤልያስ ለተጨማሪ ሦስት ዓመታት በፕሬዘዳንትነት እንዲመሩ፤
ዶ/ር ጣሰው ገብሬ በም. ፕሬዘዳንትነት እንዲመሩ፤
ሲመረጡ በዚሁ መልኩም የቤተከርስቲያኒቱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና የብሄራዊ ቦርድ አባላት ሆነው የሚያገለግሉ መሪዎች ተመርጠዋል።
እንዲሁም ላለፉት አምስት ዓመታት የቤተ ክርስቲያኒቱ ዋና ጸሀፊ በነበሩት አቶ ኩርሴ ሸፈኖ ምትክ ዶ/ር ስምዖን ሙላቱ በዋና ጸሐፊነት ሲመረጡ፤ የልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን

እንዲያገለግሉ ዶ/ር ተፈራ ታሎሬ ተመርጠዋል።

 


ይኸው የመሪዎች ምርጫ ሂደት በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ብርካታ አዳዲስ መሪዎች እንዲተኩ የተደረገበት ቢሆንም ፍጹም ሰላማዊና መላው የጠቅላላ ጉባዔ ተሳታፊ ደስ የተሰኘበት እንደነበር ታውቁዋል።
በዚሁ ጉባዔ ማጠቃለያ ላይም የቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች ለአዲሶቹ እና ተሰናባች መሪዎች ጸሎት ያደረጉ ሲሆን ጉባዔውም የጌታ እራትን አብሮ በመቁረስ እና በኅብረት ዝማሬ ፍጻሜ ሆኑዋል።