የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ምርጫ

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ፕሬዘዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ ዶ/ር ኢያሱ ኤልያስ ለሁለተኛ ጊዜ የተመረጡ ሲሆን ዶ/ር ጣሰው ገብሬ በፕሮፌሰር ብርሃኑ ቆጢሶ ምትክ በምክትል ፕሬዘዳንትነት እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል። የልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን ለመጪዎቹ አራት ዓመታት እንዲያገለግሉም ዶ/ር ተፈራ ታሎሬ በ58ኛው የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ጠቅላላ ጉባዔ ተመርጠዋል።

ዶ/ር ኢያሱ ኤልያስ
ዶ/ር ጣሰው ገብሬ

 

እግዚአብሔር በቤተክርስቲያናችን ስለተካሄደው ሰላማዊ የአገልግሎት አደራ ሽግግር ስሙ የተባረከ ይሁን። በዚሁ ጉዳይ ላይ ስትጸልዩ የነበራችሁ ወገኖችን ሁሉ እግዚአብሔር ይባርካችሁ ለማለት እንወዳለን!

 

                   ዶ/ር ተፈራ ታሎሬ